የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የምክር ቤቱን 2ኛ የስራ ዘመን 45ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::

    ክብርት አፈ-ጉባኤዋ በመግለጫቸውም ጥቅምት 22/2013ዓ.ም በምእራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዙ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ የስራ ዘመን 45ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከጥቅምት 26 እስከ 27 ድረስ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚያካሂድና በጉባኤውም የምክር ቤቱን የ44ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ ‘የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚቀርብና ውይይት እንደሚደረግበት እንዲሁም የተጓደሉ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ሹመት እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡
    በተያያዘም ከጉባኤው 1ቀን ቀደም ብሎ ማለትም እሮብ ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ለምክር ቤቱ ሴት አባላት (ኮኮስ) “ሰላምና ሴቶች” በሚል ርእስ ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
    ምንጭ፡-የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ማህበራዊ ሚዲያ ገፅ