የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርታቸውን ላቀረቡ ሴክተር መ/ቤቶች የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ተሰጠ::

    በትላንትናው ዕለት በተጀመረው የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ የስድስት ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ላይ የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንትን ቢሮ ፣ ግብርናና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ፣ ኮንስትራክሽን ቢሮ ፣ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ፣ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እንዲሁም መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ የመድረኩም ተሳታፊዎች ሪፖርቱ ላይ ሀሳብና አስተያየታቸውን ሰንዝረው ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
    ንግድ ፣ ኢንዲስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮን በተመለከተ ኢንቨስትመንት ካልተስፋፋና የስራ ዕድል በአግባቡ መፍጠር ካልተቻለ ለአስተዳደሩ ገቢ ለማመንጨት አስቸጋሪ በመሆኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጠንካራ ድጋፍ ለዘርፉ ሊያደርግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ በተለይም የስራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸሙ በዓመቱ ከሚጠበቀው አነስተኛ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
    ከመሬት ልማትና ማኔጅመነት ቢሮ ጋር በተያያዘ ስራዎችን በመመሪያ ላይ ተመስርቶ በአግባቡ ለመስራት የሚስተዋሉ የስነ ምግባርና ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ ከካሳ አከፋፈል ስርአቱ ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ለመቅረፍ መስራ ተገቢነተ እንዳለውም ተገልጿል፡፡
    የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኩልም የተሰራው የስራ ቦታ ምቹ ለማድረግ የተደረገው ጥረት መልካም መሆኑ በሌላ በኩልም መረጃ የማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በአማርኛ በኦሮምኛና በሱማልኛ የማሰራጨቱ ጉዳይ ላይ ሊታሰብበት እንደሚገባ እንዲሁም ብዙሀን መገናኛ በተመለከተ ዘርፉን እንደ አንድ የስራ ዕድል መፍጠሪያ መጠቀም በቀጣይ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ አቀጣጫ ተሰጥቷል፡፡
    ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮን በተመለከተም በአስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በማጥናት በየተቋማቱ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ግብአትና አስፈላጊ ግብአቶችና ድጋፎችን ሊሰጥ እንደሚገባ ተጠየቁሟ፡፡ በሰራተኛ ምደባ በኩል የሚስተዋሉ ችግሮችንም ለመቅረፍ ጠንካራ ስራ እንደሚስተዋል ተገቢነት አለው ተብሏል፡፡
    በዛሬው ዕለትም ጤና ቢሮ፣ ትምህርት ቢሮና ሌሎች ሴክተር ተቋማት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን በማቅረብ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል