እየተካሄደ በሚገኘዉ የአስተዳደሩ የአስፈፃሚ አካላት የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በማህበራዊ ዘርፍ የትምህርትና የጤና አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ::

    በትላንትና እለት የተጀመረው የአስተዳደሩ የአስፈፃሚ አካላት የ2013 በጀት ዓመት የስድስት ወር የስራ አስፈፃሚ ግምገማ ዛሬ ከሰዓት የማህበራዊ ዘርፎች መካከል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ፣የጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ አቅራቢነት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡
    የአስተዳደሩ የአስፈፃሚ አካላት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረኩን የመሩት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህና ምክትል ከንቲባ የንግድ ኢንደስቲሪና ኢንቨስትምንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከዲር ጁሃር በማህበራዊ ዘርፍ የትምህርትና የጤና የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ጥሩ መሆኑን ገልፀው ዝቅተኛ አፈፃፀም ላይ የሚገኙ ተግባራትን ለማሻሻል ያላቸዉን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ለተሸላ ዉጤት መስራት እንዳለባቸዉ ጠቁመዋል፡፡
    የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በሰጡት አስተያየት በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከሁለቱ ተቋሟት ጎን ሁሉም የአስተዳደሩ አራሮች፣ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ እንዲሁም መላዉ ህብረተሰብ ተማሪዎች የጥንቃቄ ተግባራትን በሚገባ እንዲተገብሩ በማድረግ የበኩላችንን የዜግነት ድርሻ እንወጣ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
    የአስተዳደሩ የአስፈፃሚ አካላት የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማዉ በነገው እለትም ቀጥሎ ይውላል፡፡