በየደረጃው የሚገኙ የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፤ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

    በአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና፣ የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በተመራው መድረክ፤ የውይይት መነሻ ነጥቦች ቀርበው፤ አካታች አገራዊ ምክክር አስፈላጊነት ላይ እና ሌሎች ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው ተወያይተዋል።
    ሀገሪቱን ለማፍረስ በተነሱ የኢትዮጵያ ጠላቶች ላይ በተነሳው ህዝባዊ ማዕበል የመጀመሪያው ምዕራፍ ድል መመዝገቡንና፤ ያለመስዋዕትነት የሚመጣ ሰላም ስለሌለ ኢትዮጵያዊ አንድነቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቶ፤ ትኩረት የሚሹ አገራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በመለየት፤ ከመድረኩ ቀጣይ የጉዞ አቅጣጫ ተቀምጧል።
    ይህ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረገው ውይይት እስከ ታችኛው የህብረተሰብ ክፍል የሚወርድ ሲሆን፤ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኅዳር 30 ባደረገው ስብሰባ፤ የአገርን ኅልውና ለማጽናትና ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማሰቀመጡ ይታወሳል።