የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት፤ 3ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አመት 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል። ምክር ቤቱ በጉባኤው የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋምና፣ ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣ አዋጅ፤ የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ፤ እንዲሁም የከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት አፅድቋል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው የሚከተሉትን ዕጩዎች
1- አቶ ሻኪር አህመድ፣
2- አቶ ደረጀ ፀጋዬ እና
3- አቶ ገዛኸኝ ታዲዮስ፣ በአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ እንዲሆኑ ሲሾም፤
1- ደቻስ ኡስማኤል፣
2- አብዱልማሊክ መሀመድ፣
3- ሮቤል አለማየሁ፣
4- ፈቲያ በያን፣
5- አብዱልፈታህ ጣሂር እና
6- ባይሳ ጅሩ የአስተዳደሩ ይግባኝ ሰሚ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ሆነው እንዲሾሙ ም/ቤቱ አፅድቋል።
ከዚህ በተጨማሪ 28 የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት፤ በ7 የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ አባል እንዲሆኑ ሹመታቸው ፀድቆ፤ ሁሉም ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።


