#ድሬዳዋ ልጆቿን በናፍቆት እየጠበቀች ነው።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች፤ እናት ሀገራችን ሰው በፈለገችበት ጊዜ አለንልሽ ብለው፤ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን በማስመስከር ወደ ቤታቸው መግባት ጀምረዋል። ወንድም-እህቶቼ እንኳን በደህና መጣችሁ። ውቧ እናታችን ድሬዳዋ፤ እንደአቅሟ ለልጆቿ አቀባበል ማጀቷን አሟልታለች። ኑ፤ የናፈቃችሁን የእናታችሁን የፍቅር ማዕድ ተቋደሱ፤ የዘመናት የናፍቆት እንባዋንም አብሱ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።