መስከረም 16 ቀን 2015 የኤስ ኦ ኤስ ህጻናት መንደሮች ሀረር ቅርንጫፍ ከድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ፣የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር ለ210 የጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለ150 አካል ጉዳተኛ ልጆች የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
የSOS ህፃናት መንደር በከተማው በሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች እና አካል ጉዳተኛ ህጻናትን ለመደገፍ እየሰራ ያለ የአለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን “አንድም ልጅ ብቻውን ማደግ የለበትም” እና አንድም ልጅ የትምህርት ቁሳቁስ በማጣት እቤት ውስጥ መቀመጥ የለበትም” በሚል መሪህ ቃል ” 1600 ደብተር፣ 1032 እርሳስ፣743 ብዕር ፣516 መቅረጫዎች. ፣ 258 ላጵስ 180 ቦርሳዎች ባጠቃላይ ከ500 ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ የትምህርት ቢሮ የኃላፊ አቶ አቡበከር አብዶሽ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተውካይ ወይዘሮ ናኢማ አብዱረህማን፣የድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስእና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ተወካይ ወይዘሮ ስሜነሽ አለማየሁ እና የተማሪዎች ቤተሰቦች በተገኙበት ነው ይህ ድጋፍ የተደረገው።
“የSOS ህጻናት መንደር” የድሬዳዋ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ሚካኤል ስንታየሁ እንዳሉት ድርጅቱ በድሬዳዋ ከተማ ለ3-5 ዓመታት ህጻናትን ከጎዳና በማንሳት እና አካል ጉዳተኞችን በመርዳት ላይ ከአስተዳደሩ ጋር በመሆን ሁለት ፕሮጀክቶችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ፣ ህጻናትን በማስተማር እና በማሳደግ ላይ በትኩረት በመስራት ከ3ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን መሰል ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ም/ል ኃላፊ አቶ አቡበከር አብዶሽ እንደተናገሩት “ሀገራችን ወደ ብልፅግና ልትሸጋገር የምትችለው በእውቀት እና በክህሎት የተገንቡ ዜጎችን ማፍራት ስንችልና አገራችን ከተባበሩት መንግስታት ጋር የተፈረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ስናደርግ ብቻ ነው፤ በመሆኑም ዜጎቻችን ሁሉ የትምህርት እድል ኢንዲያገኙ ዘንድ በዚህ የበጎ ፈቃድ ስራ ላይ ለተሳተፉት ሁሉ በትምህርት ቢሮው እና በአስተዳደሩ ተማሪዎች ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲል ተናግሯል።
በኤልያስ አሜ
ፎቶ፡ አብይ ሽመልስ


