ህወሓት ለሦሥተኛ ጊዜ በሀገር ሉአላዊነት ላይ የከፈተውን ጦርነት በጠንካራ አመራር ለመቀልበስ ሲባል የወጣ የብልጽግና ፓርቲ ጊዚያዊ የስነምግባር ጋይድላይን ዙሪያ የአስተዳደሩ አጠቃላይ አመራሮች ተወያዩ።
ጋይድ ላይኑ ህወሓት ለሦሥተኛ ጊዜ በሀገር ሉአላዊነት ላይ የጋረጠውን የጦርነት አደጋ በአስተማማኝ የአመራር መስተጋብር መቀልበስ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የጦርነቱ ኢ-ተገማች ሁኔታዎች በአመራር የስራ ተሳትፎ ላይ ተሻጋሪና ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ፣ ከአመራሩ ቀጥተኛ ተሳትፎ ውጭ አገር የተደቀነባትን የህልውና አደጋ መከላከልም ሆነ መቀልበስ በጣም አዳጋች በመሆኑ፣ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋርም ሆነ በየደረጃው የህልውና ዘመቻው ከሚፈልገው ወሳኝ፣ አስቸኳይና አጣዳፊ…


