ጋይድ ላይኑ ህወሓት ለሦሥተኛ ጊዜ በሀገር ሉአላዊነት ላይ የጋረጠውን የጦርነት አደጋ በአስተማማኝ የአመራር መስተጋብር መቀልበስ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የጦርነቱ ኢ-ተገማች ሁኔታዎች በአመራር የስራ ተሳትፎ ላይ ተሻጋሪና ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ፣ ከአመራሩ ቀጥተኛ ተሳትፎ ውጭ አገር የተደቀነባትን የህልውና አደጋ መከላከልም ሆነ መቀልበስ በጣም አዳጋች በመሆኑ፣ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋርም ሆነ በየደረጃው የህልውና ዘመቻው ከሚፈልገው ወሳኝ፣ አስቸኳይና አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ፈጣን የሆነ የወዲያው ምላሽ መስጠት ስለሚያስፈልግ፣ ጦርነት በጥብቅ ዲሲፕሊን ካልተመራ በደቂቃዎች ሽርፍራፊ የዲሲፕሊን መጓደል የሚደርሰው ኪሳራና ብሄራዊ ጉዳት በጣም አደገኛና በቀላሉ ሊቀለበስ የማይችል ስለሆነ፣ የአመራሩ የዲሲፕሊን ሁኔታ ከመቸውም ጊዜ በላይ በጣም አስፈላጊና የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ስለሆነ፣ በዚህ ወቅት ማንኛውንም ስህተት በቸልተኝነት ወይም ሆን ብሎ መፈጸም ይቅር ሊባል የማይችል በመሆኑ፣ አጠቃላይ ጦርነቱንና ተያያዥ ጉዳዮችን በታወቀ የስነምግባር ጋይድ ላይን መምራት ስለሚያስፈልፈግ ይህ ጊዚያዊ የስነምግባር ጋይድ ላይን ሊወጣ የቻለ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የተከበሩ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ገልጸዋል።
አክለውም ጋይድ ላይኑ ከነሓሴ 25 ቀን 2014 ጀምሮ ለሦሥተኛ ጊዜ በህወሓት የተከፈተው ጦርነት አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ እስኪቀለበስ ድረስ በሁሉም የፓርቲ መዋቅር ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር በየደረጃው የተቋቋሙ ጊዚያዊ አደረጃጀቶች ወይም ኮሚቴዎችን ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ግዴታን በብቃት አለመወጣትና ተልዕኮን ማንጠባጠብ እንዲሁም በውጤት አለመታገዝ ደረጃውን የጠበቀ ማስጠንቀቂያ የሚያሰጥ መሆኑን ገልጸው ዲስፕሊን የሌለው አመራር አይጠቅመንም የአሸባሪውን ህወሃት አላማ ለመቀልበስ ለወጣው ጊዜያዊ ጋይድላይን መመራት የግድ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
ምንጭ:-
የድሬዳዋ ብልጽግና ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት


