ፀሎተ ሀሙስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በፆም፣ በፀሎትና በስግደት የሚከበረው ፀሎተ ሀሙስ በዛሬው ዕለትም በድሬዳዋ ቅድስት ማሪያም ካቴደራል ቤተክርስትያን በተለያዩ ስነ-ስርአቶች ተከብሯል ።

በዚህም ክርስቶስ ዝቅ ብሎ የሀዋርያቱን እግር በማጠብ ትህትናውን የገለፀበትን ተግባር በማሰብ “ህጽበተ እግር” ተከናውኗል።

በፀሎተ ሀሙስ እየሱስ ክርስቶስ ታላቅ መንፈሳዊ ሚስጥርን የገለጠበት በፀሎት መትጋትንና ትህትናን በተግባር ያስተማረበት እንደሆነም ቀሲስ ደበበ ተመስገን ተናግራዋል።

በአሉን ስናከብርም በፍፁም ትህትና እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን ይገባል በማለት ቀሲስ ደበበ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የዛሬው ዕለት እየሱስ ክርስቶስ የደቀመዛሙርቱን እግር ያጠበበትና ትህትናን የገለፀበት እለት በመሆኑ እኛም እርስ በእርስ በመከባበርና በመረዳዳት እለቱን ልናሳልፍ ይገባል በማለት የተናገሩት ደግሞ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ምዕመናን ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *