በሰሜን ዕዝ በሚገኙ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የጁንታው የህውኃት ኃይል ካደረሰው አሳፋሪ ጥቃት ጋር ተያይዞ ጉዳት ለደረሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የገና በዓልን በማስመልከት የአማን ሆቴል አስተዳደሪ የሰንጋ ድጋፍ አደረጉ፡፡ በድጋፉ ላይ የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ኢንስፔክተር ተዘራ የተደረገው ድጋፍ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ እስቅያስ ታፈሰ እንዳሉት በጁንታው የህውኃት ኃይል በተወሰደው ህግን የማስከበር ሂደት ጉዳት ለደረሰባቸው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የአስተዳደሩ ነዋሪ ህብረተሰብና ባለሀብቱም በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ኃላፊ የሆኑት ኮሮኔል ብርሀኑ ዘመዴ ለተጎዱ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በአስተዳደሩ ፣ በማህበረሰቡና በባለሀብቱ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ አመስግነው በቀጣይም ህብረተሰቡና ባለሀብቱ ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው እንዲቆምና አጋርነቱን እንዲያሳያቸው ጥሪአቸውን አስተላልፈዋል፡፡


