ዜጎች በመንግስት ተቋማት የሚፈልጉትን አገልግሎት በጥራትና በጊዜ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

    የድሬደዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በአስተዳደሩ ካሉ የመንግስት ተቋማት ጋር የ 6ወር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አፈታት በተመለከተ የእቅድ አፈፃጸም ግምገማ አካሄደ ፡፡
    በምክክር መድረኩ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ለማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ እንደተናገሩት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በእቅድ በመመራቱ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ህዝቡ የሚጠብቀውን አገልግሎት እንዲያገኝ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየጊዜው መፈተሽ የመልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡
    ኃላፊው ከዚህም ጋር በማያያዝ አመራሩና ፈፃሚ ባለሞያዎች ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት በአጭር ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ አገልግሎት አሰጣጣቸውን በቅንነት ፣ በስነ ምግባርና በተነሳሽነት አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን ፍላጎት ማርካት ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
    ኃላፊው አክለውም በቅንጅትና በክትትል አገልግሎት የማንሰጥ ከሆነ ሀጋራችን የዲሞክራሲና የሀገር ግንባታ ህዝቡ እንዲጠራጠር ከማድረጉም በተጨማሪ ህዝቡ መንግስትን እንዲጠራጠር ያደርጋል ብለዋል፡፡
    የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ወርቅነህ በበኩላቸው እንደተናገሩት ቀደም ሲል በመንግስት ቢሮዎች ፤ ፅ/ቤቶች፤ ጤና ተቋማትና ቀበሌዎች የመስክ ምልከታ በማድረግ የግብረ መልስ እንዲሰጥ መደረጉን በመጠቆም በቀጣይ ጊዜያትም ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተቋማት በመፍታት ህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎ እንዲያገን ተከታታይነት ያለው ምልከታቸውን እናደርጋለን ብለዋል፡፡
    አቶ ብሩክ ከዚህም ጋር አያይዘው የመንግስት ተቋማት ያሉ አገልግሎት አሰጣጥ የመንግስት ሰራተኛውና አመራሩ በስራ ቦታው አለመገኘት ትልቁ የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆኑ በቀጣይ ችግሩን ለመፍታት በተቋማት ከብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ጋር በመቀናጀት ድንገተኛ ሱፐርቪዥን በማድረግ ተገልጋዩ ህብረተሰብ በጊዜና በወቅቱ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡
    አቶ ብሩክ አክለውም በአስተዳደሩ ያሉ ትላልቅና አነስተኛ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የመንግስት ተቋማት ያላቸውን የስራ አፈጻጸም በየጊዜው የምክክር መድረክ በመፍጠር የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የምንፈታበት መድረኮችን ትኩረት ሰተን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡