የሀገር መከላከያ ሠራዊት ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በመመልመል ሲያሰለጥናቸው የቆየውን ምልምል ወታደሮች በዛሬው እየስመረቀ ይገኛል።
በመመረቅ ላይ የሚገኙት ምልምል ወታደሮች ሁርሶ፣ ጦላይና ብርሸለቆ በሚገኙ የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።
ሰልጣኞቹ በፍላጎታቸው ወደ መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀልና መስፈርቱን በሟሟላት በዛሬው ዕለት በየማሰልጠኛ ተቋሙ በመመረቅ ላይ እንደሚገኙ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።
ተመራቂ ምልምል ወታደሮቹ የአካል ብቃት ፣የተኩስና የስልት ስልጠናዎችን በመውሰድ ከፍተኛ አቅም መገንባታቸውን በተግባር ማሳየታቸው ተገልጿል፡፡
ምንጭ:- ኢዜአ፣ አብመድ


