የከተራ በአል በድሬደዋ በድምቀት ተከበረ::

    ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ማደሪያቸው በሰላም ደርሰዋል።
    የጥምቀት በዓል በየአመቱ በሀገራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በአደባባይ ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነው። የበዓሉ አከባበር የሚጀምረውም ጥር 10 ቀን ሲሆን እለቱም ታቦታት ከመንበራቸው ተነስተው ወደ ማደሪያቸው(ጥምቀተ ባህር) የሚሄዱበት እለት ነው ።በነገው እለትም የጥምቀት በአል ተከብሮ ይውላል።