በ 69 ሚሊዮን ዶላር በድሬ ደዋ እየተገነባ የሚገኘው የደረቅ ወደብ ግንባታ 50% መድረሱ ተገለፀ::

    በድሬዳዋ ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ የተመራ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን ቡድን በድሬደዋ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘውን ደረቅ ወደብ ያለበትን ሁኔታ ጎበኙ ፡፡
    በዚህ ጉብኝት ላይ ከንቲባ አህመድ እንደገለፁት በድሬዳዋ ደረቅ ወደብ በግንባታዉ ለባርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ከፈጠረው በላይ ግንባታው ተጠናቆ ሲራ ሲጀምር ከዚህ በላይ የስራ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ የድሬዳዋና የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ለውጥ በመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ አስተዳደሩ እየተከታተለው መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
    የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሎጂስቲክ ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረትዓብ ተክሉ በበኩላቸው ይህ በድሬደዋ እየተገነባ የሚገኘው ደረቅ ወደብ በ 69 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በ 34 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ደረቅ ወደብ ተጠናቆ ሲራ ሲጀምር እስከ 4 ሺ ኮንቴነር ማስተናገድ እንደሚችል ገልፀው በአውሮፓውያኖቹ አቆጣጠር ጁን 20-2020 ግንባታው የተጀመረ እና በ 15 ወራት ለማጠናቀቅ ውል የተገባ መሆኑን አብራርተው አሁን ግንባታው 50% መድረሱን ገለፀዋል ፡፡