ሳምንታዊ የጽዳ ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል

    የድሬዳዋ አስተዳደር “ከተማ አቀፍ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ” በተመረጡ የከተማ ቀበሌዎች ጫት ተራ፣ ችግኝ ጣቢያ እና ጀርባ ሰፈር አካባቢዎችን በማፅዳት ተከናውኗል።
    የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት “የከተማ ጽዳትና ውበት የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ ካልታከለበት፤ በአንድ እጅ ማጨብጨብ ነው የሚሆነው” ያሉ ሲሆን፤ በህብረተሰቡ ውስጥ በሚፈለገው መጠን የባለቤትነት ስሜት ሊስተዋል እንዳልቻለም ገልፀዋል።
    ከንቲባው ስለድሬዳዋ መቆሸሽ ማውራት ብቻውን ከተማዋ ፅዱ እንድትሆን ስለማያደርግ፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የባለቤትነት ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበው፤ “ድሬዳዋችን ደጃፉ ሲፀዳ ቆሞ የሚታዘብ ነዋሪ ትናንትና አልነበራትም፤ ወደፊትም ማየት አትፈልግም” ብለዋል።