በድሬዳዋ አስተዳደር ከአዲስ ምዕራፍ ወዲህ የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና የልማት ስራዎች ከሌላው ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እየተካሄደ ያለበት ሁኔታ የተፈጠረ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ በአስተዳደሩ 16ኛ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በደመቀና ያለ ምንም እንከን የተከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ በአስተዳደራችን ፀረ-ሠላም ሃይሎች አስተዳደራችንን ለመፈታተን የሞከሩ ቢሆንም የአስተዳደሩ የመንግስት አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠትና ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑን እያሳወቅን የአሁናዊ የአስተዳደራችን ሁኔታ ፍጹም ሠላማዊ መሆኑን እየገለጽን የአስተዳደራችን ነዋሪዎች መሠረታዊ የልማት ስራችሁን በማከናወን የአካባቢያችሁን ሠላም በንቃት በመከታተል የተለየ ነገር ካለ ብቻ ለፍትህ አካላት መረጃ እንድታደርሱ እንላለን፡፡


