በድሬዳዋ አስተዳደር ከልማት ጎንለጎን ለሠላምና ፀጥታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ዛሬ በወቅታዊ ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በተካሄደው የምክክር መድረክ ተገለፀ።
በምክክር መድረኩ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የፓርቲው ምክትል ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድና የፍትህ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሊኖራቸው በሚገባው ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።


