ይህን መሰሉ ሀገርን የታደጉ ጀግኖችን የመጠየቅና ድጋፍ የማድረግ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልፃል::
በኢ/ፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ኮልፌ ማሰልጠኛ በተካሄደው የድጋፍ ስነ-ስርአት ላይ ንግግር ያደረጉት የድ/ዳ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለሀገርና ህዝባችሁ ስትሉ በህልውና ዘመቻ በተሰለፋችሁበት ግንባር ሁሉ መስዋትነት በመክፈል በጀግንነት የሽብር ቡድኖች ሽንፈት እንዲከናነቡ በማድረግ ሀገራችሁን ታድጋችሃል እና ትልቅ ክብር ይገባችሃል ነው ያሉት::
ከንቲባ ከድር አያይዘውም አስተዳደሩና የድሬደዋ ፖሊስ እንዲሁም መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ ሁሌም ከጎናችሁ ነው ይህም ድጋፍ ይህንኑ የሚያሳያና የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል::
የኢ/ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው የፌደራል ፖሊስ ለሀገር ሰላምና ደህንነት መረጋገጥና ለዜጎች መብት መከበር የህይወትና የአካል መስዋትነት ጭምር በመክፈል ሞያዊና ተቋማዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሄነ ተናግረው በተለይ በሀገር የህልውና ዘመቻ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ላይ የህይወትና የአካል መስዋትነቶችን ጭምር በመክፈል አሸባሪውን የህውሀትና የሸኔ ቡድኖችን በመደምሰስ አኩሪ ድሎችን መግናፀፍ ተችሏል ነው ያሉት::
ይህንንም ታላቅ ጀግንነት ታሪክ ሁሌም ሲዘክረው ይኖርል ያሉት ም/ኮሚሽንር ጀነራሉ የድሬደዋ አስተዳደርና ድሬድዋ ፖሊስ ለሰራዊቱ ላሳየው ወገናዊ ደጀንንትና ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
ሀገርን በጀግንነት መጠበቅ ህዝብን በሰብአዊነት ማገልገል ትልቅ ክብርና እድለኝነት ነው ያሉት የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው የድሬደዋ ፖሊስ ከአስተዳደሩ ጋር በመሆንና መላው የቀጠና ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም የተለያዩ የስራ ክፍሎች፣መላው ህ/ብን ፣ባለሀብቶችንና ደጋፍ አድራጊ ድርጅቶችን በማስተባበር በአጭር ግዜ ውስጥ ይህ ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር በላይ የሆነ ድጋፍ ሊሰባሰብ ዛሬ በድጋፍ ሊበረክት መቻሉን ተናግረዋል ::
ኮሚሽነር አለሙ መግራ አክለውም ይህ አይነቱ ድጋፍና እናንተ ሀገርን ያስቀጠላችሁ ጀግኖችን በቤተሰባዊንት የመጠየቅ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናሉ ያሉ ሲሆን ይህን የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ ላስተባበሩ ላገዙና ለደገፉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
በእዚሁ የድጋፍ ስነ-ስርአት ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው አርባ አምስት ሰንጋ በሬዎች፣ምግብና የምግብ ፍጆታዎች ፣የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችና አልባሳት፣መጫሚያ ነጠላ ጫማዎችና ሌሎች መሰል ድጋፎች ነው ርክተዋል::


