‹‹ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውጤታማነት ለማረጋገጥ እንሰራለን ››፡፡

    ኢንጅነር መሀዲ መሀመድ
    የድሬደዋ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
    ዳይሬክቶሬቱ በቀጣይ ከባለድርቫ አካላት ጋር በቀጣይ የተቀላጠፈ ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍጠር ምክክር አካሂዷል
    የከንቲባ እና የካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ እና የህዝብ አቤቱታ ቅሬታ አፈታት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽኩሪ አብዱረማን በምክክር መድረኩ ባስተላለፉት መልእክት ሀገራዊ የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ከድህነት ወደ ብልጽግና በሚደረገው ጉዞ የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ዋና መሳሪያ እንደመሆኑ መጠን ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማጎልበት ለሀገራችን ብሎም ለአስተዳደሩ ኢኮኖሚ እድገት እንዲውል ለማድረግ የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
    የአስተዳደሩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ኢንጅነር መሀዲ መሀመድ ከዚህ በፊት በነብው አስራር በዘርፉ ባሉ ተዋናዮች መካከል የተናበበ እና የተቀናጀ አሰራር ባከመኖሮ የተፈለገውን ያክል ውጤት ለማስመዝገብ አለመቻሉን ጠቁመዋል፡፡
    ይህንን ለመቅረፍ የተለያ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ከ (UIIDP) Urban Institutional and Infrastructure Development Program ጋር በመተባበር ለቴክኖሎጂ ስራ ውጤቶች ሽግግር እና በቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያተኮረ ምክክር በአስተዳደሩ ላሉ የፈጠራ ባለቤቶችና ለባለድርሻ አካላት ጋር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ መሆኑን የገለጹት የአስተዳደሩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀዲ መሀመድ በቀጣይ የታቀዱ እቅዶችም በጋራና በቅንጅት በመስራት ውጤታማ እንዲሆኑ ይህ የምክክር መድረክ መካሄዱ የጎላ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡
    የቴክኖሎጂ ነክ ስራ ፈጠራዎች ሽግግር ሂደቶች እና አእምሮአዊ ንብረት አጠባበቅና አስተዳደር በተመለከተ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡