ህገ ወጥ ንግድን በመከላከል ከተማውን መልካም ገጽታ ለማላበስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

    በደንብ ማስከበሩ ሂደት ማህበረሰቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡
    ድሬዳዋ ከተማ ታሪኳ አንደሚያስረዳን ጽዱና ውብ ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት በተለያዩ ምክንያቶች ከተማችን ገጽታ በሚፈለገው መጠን ጥራቱን የጠበቀ መሆን አልቻለም፡፡
    በአስተዳደሩ የከተማዋን ገጽታ እያበላሹ ካሉ ምክንያቶች አንዱ ህገ ወጥ ንግድ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ባለው ተግባር መልካም ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፋሚ ሙሜ ይገልጻሉ፡፡
    በዚህ ስፍራ በነበረው ህገ ወጥ ንግድ ለአካባቢው ነዋሪ ጭምር አዳጋች ሁኔታን ፈጥሮ እንደነበር አቶ ፋሚ ይናገራሉ፡፡
    የቀፊራ ክፍት የገበያ ማእከል ሌላው የደንብ ማስከበር ስራ የተከናወነበት ስፍራ ነው በስፍራው ጅግ ስርአት አልባ የንግድ ስርአት እንደነበር የደንብ ማስከበር ስራ ላይ የተሰማሩት ሰብለ ንጉሴና ባልደረበቿ ይገልጻሉ፡፡
    በቀፊራ አካባቢ የተሰራው የደንብ ማስከበር ተግባር ስፍራውን ለግብይት ምቹ ከማድረግ ባለፈ ለህገ ወጥ ድርጊትን መካከል ያስችላል ሲሉ በማእከሉ ሲገበያዩ ያገኘናቸው ተጠቃሚዎች ይናገራሉ፡፡
    በእርግጥ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ህገ ወጥ ንግድን በመከላከል የከተማዋን መልካም ገጽታ ለመገንባት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡
    በቀጣይ በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችን በማይጎዳ መልኩና ስልታዊ በሆነ ሁኔታ በከተማዋ ህገ ወጥ ንግድ በሚከናወንባቸው ስፍራዎች የደንብ ማስከበር ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል እንደሚቀጥል የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊው አቶ ፋሚ ጠቁመዋል፡፡