አክብረው በአንድነት ያቆዩዋቸውን እሴቶቻቸውን አጠናክሮ መቀጠልም ሰላማዊ የሆነ ማህበራዊ መስተጋብርና ጠንካራ ሀገራዊ መግባባትን ይፈጥራል።
ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብቻ ሳይሆኑ የሀገር ሀብት እና የአንድነት መሰረት መሆናቸው ብዙዎችን የሚያስማማ ጉዳይ ነው። እነዚህን የሀገር ሀብቶች ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ሳይበረዝ ለትውልድ ማስተላለፍ ቀጣይዋን ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ለመገንባት አበርክቶው ከፍ ያለ ነው።
ሁሉም ሐይማኖት የሚያስተምሯቸው እና የሚያጎናጽፋቸውን መቻቻልን፣ አብሮነትን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን እና እርስ በእርስ መተሳሰብን ነው፡፡ስለሆነም እያንዳንዳችን ከሐይማኖቶቻችን የምንማረውን በገሀዱ ዓለም ልናሳይ ይገባል፤ይህ ሲሆን ትርጉሙ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡
በዓላት በህዝቦች መካከል መቀራረብን ያጠናክራሉ፤ ማህበራዊ ትስስርና አንድነትን ይፈጥራሉ። እያንዳንዱ ሰው ሲከወን ያየውን ባህል የእኔ ነው የሚል ስሜት እንዲኖረው ያደርጋሉ።


