የድሬዳዋ አሰተዳደር የብልጽግና ሴቶች ሊግ ከአሰተዳደሩ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በመከላከያ ሆስፒታል ግቢ በመገኘት ከጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር የመስቀል በዓል አክብረዋል።

    በክብረ በአሉ ላይ የአሰተዳደሩ ም/ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈትሂያ አደን፣ም/አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ፣ የድሬዳዋ አሰተዳደርሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ የተገኙ ሲሆን ለጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የበአል ስጦታ በማበርከትና በዓሉን በጋራ በማክበር ሁሌም ከጀግኖቹ ጎን መሆናቸዉን አረጋግጠዉላቸዋል።
    ” ለሀገር ክብር በአንድነት እናብር ”