የጤና ሚኒስቴር ምኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች በድሬዳዋ አስተዳደር ተገኝተው የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታልን፤ የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከልን እንዲሁም በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል እየተገነባ ያለውን የዲያሊሲስ/ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጫ ማዕከልን፤ በሆስፒታሉ የህሙማን ቅብብሎሽ ስርዓቱን ለማዘመን የሚረዳውን የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት(EMR) እና ሥራ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘውን የሱስ ማገገሚያ ማዕከልን ከድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከክቡር ከድር ጁሃር፤ ከምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህና ከሌሎች ሥራ ኃላፊዎች ጋር የጎበኙ ሲሆን ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ተቋማቱን አመራሮችና ባለሞያዎችን በማበረታታት ሚኒስቴር መሥሪያቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ምኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡


