የኢትዮጵያ ጀግኖች የጦር አካል ጉዳተኞች የተሃድሶ እና ሥልጠና ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ ለመንግሥት ቀርቧል፦ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

    ለሀገር ኅልውና እና ደህንነት ዋጋ የከፈሉ እና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጀግኖቻን ክብር ከፍ የሚያደርግ እና ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያስችል የኢትዮጵያ ጀግኖች የጦር አካል ጉዳተኞች የተሃድሶ እና ሥልጠና ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ ለመንግሥት መቅረቡን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ።  ሚኒስትሯ ይህን የገለጹት ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን…

    Read More

      የጤና ሚኒስቴር ምኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

      የጤና ሚኒስቴር ምኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች በድሬዳዋ አስተዳደር ተገኝተው የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ክብርት ሚኒስትሯ የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታልን፤ የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከልን እንዲሁም በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል እየተገነባ ያለውን የዲያሊሲስ/ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጫ ማዕከልን፤ በሆስፒታሉ የህሙማን ቅብብሎሽ ስርዓቱን ለማዘመን የሚረዳውን የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት(EMR) እና ሥራ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘውን…

      Read More

        <<አካታች የፈጠራ የስራና ሽግግራዊ መፍትሄ ለኢትዮጰያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት >> በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ 30በአገር አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን በዛሬው እለት በፖናል ውይይት ተከብሮ ውሏል።

        በነገው እለትም የፌደራልና የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ መረሀ ግብሮች በአሉ እንደሚከበር ለማወቅ ተችሏል።

        Read More

          የዜጎችን ደህንነትና የከተማዋን ውበት ለመጠበቅ ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል ተባለ

          በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአስተዳረሩ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች፣ የሂደትና የቀበሌ አመራሮች፣ ከፈተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰቷል፡ በስልጠናው ላይም ፅ/ቤቱ እንደ ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን በ2006 ዓ.ም የተመሰተረተ ሲሆን በአስተዳደሩ ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 33/2006 የተቋቋመ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድና…

          Read More

            የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር ሕዳር 24/2015 በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ተገለፀ።

            ዘንድሮ ለ30ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በአስተዳደሩ ህዳር 24 /2015 ዓ.ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ማህበሪዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግላጫ አስታውቀዋል፡ በዓሉ «አካታች የፈጠራ ስራ እና ሽግግራዊ መፍትሄ በኢትዮጱያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት» በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ኃላፊዋ…

            Read More

              የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አጎራባች ዞኖች የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ተካሄደ።

              የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አጎራባች ዞኖች የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ በሶማሌ ክልል ሊባን ዞን ጉሬ ዳሞሌ ወረዳ ተካሂዷል። በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን እንዲሁም የባሌ ዞን እና ሊበን ዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ጅብሪ እና በሶማሌ ክልል በጉራ-ዳሞ ኦሌ ወረዳዎች የሚኖሩ የኦሮሞና ሶማሌ ወንድማማች…

              Read More

                የድሬደዋ አስተዳደርና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለቀጣይ 3 ዓመታት በተለያዩ መስኮች ላይ በጋራ አቅደው በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

                የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በተለያዩ መስኮች ተቀራርቦ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በተለይም ካለፋት ሦስት ዓመት ወዲህ በተለይ በአቅም ግንባታ ፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ለቀጣይ ሦስት ዓመት የሚቆይና አስተዳደሩን ድህንትና ስራአጥነትን በመቀነስ ልማትና እድገት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚያግዙ ስራዎች በተለያየ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ላይ በጋር መስራት እንዲያስችላቸው የጋራ…

                Read More

                  17ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ” ፌደራሊዝም፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትና ህገ-መንግስታዊ ” በሚል ርዕስ የተለያዩ ምሁራንና የህብረተሰብ ተወካዮችን ያሳተፈ የቶክሾዉ ፕሮግራም ተዘጋጀ

                  ህዳር 29 ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ በድሬዳዋ አስተዳደር መገናኛ ብዙሀን ድርጅት፣ በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤትና በድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የጋራ አዘጋጅነት “ፌደራሊዝም፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትና ህገ-መንግስታዊ ” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል። በቶክ ሾዉ ፕሮግራሙ ላይ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የህግ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ…

                  Read More

                    የ17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ

                    የተከበራችሁ መላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች እና የሀገራችን ዜጎች “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀት ለምናከብረው 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን! በመቀጠልም ሕብረ ብሔራዊ ብዝሃነት ባለባቸው እና ሕገ-መንግሥታዊ ዕውቅና በሰጡ ሀገራት የተዘረጋውን የፌደራል ሥርዓትን ስንመለከት ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዓላማዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በዋናነት ከማንነት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ…

                    Read More

                      የድሬዳዋ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ

                      በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሕብረብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር የቆየ ሲሆን በዛሬው እለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ በአስተዳደሩ የሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የሰው ሀብት ኃላፊዎች እና ከሁሉም የአስዳደሩ የመንግስት ተቋማት የተወጣጡ የመንግስት…

                      Read More