የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር ሕዳር 24/2015 በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ተገለፀ።

    ዘንድሮ ለ30ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በአስተዳደሩ ህዳር 24 /2015 ዓ.ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ማህበሪዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግላጫ አስታውቀዋል፡ በዓሉ «አካታች የፈጠራ ስራ እና ሽግግራዊ መፍትሄ በኢትዮጱያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት» በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ኃላፊዋ አክለው በመግለፅ በአሉ ህዳር 23 እና 24/2015 በተለያዩ መርሀ ግብር ይከበራል ብለዋል።

    በዚህም መሰረት በ23/2015 በሚካሄደው የፓናል ውይይት በውይይቱ አካል ጉዳተኞች ‌፡ የተለያዩ አጋር ድርጁቶች እንዲሁም የመንግስት አካላት የሚሳተፉበት ይሆናል ብለዋል፡፡ እንዲሁም ህዳር 24/2015 ዓ/ም የተባበሩት መንግስት ተወካዮች፡ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች፡ ሚኒስትሮች እና የአስተዳደራችን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የማጠቃለያ ፕሮግራም እንደሚካሄድ ገልፀዋል፡፡

    በመጨረሻም የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ማህበሪዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን በመግላጫቸው እንዳሳወቁት በዓሉ ስናከብር የድሬዳዋ ህዝብ እንግዳ ተቀባይነቱ ቀደም ሲል የሚታወቅ መሆኑን አውስተው፤ በከተማችን የተለያዩ ከ300 በላይ እንግዶች በአሉን ለመታደም ስለሚመጡ ማህበረሰቡ ድሬ የምትታወቅበትን እንግዳ ተቀባይነታችን እንግዶቻችን በሰላም እንድትቀበሉልን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም ለመላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡