በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአስተዳረሩ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች፣ የሂደትና የቀበሌ አመራሮች፣ ከፈተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰቷል፡
በስልጠናው ላይም ፅ/ቤቱ እንደ ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን በ2006 ዓ.ም የተመሰተረተ ሲሆን በአስተዳደሩ ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 33/2006 የተቋቋመ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኤፍሬም ግርማይ አብራርተዋል፡፡ ከተመሰረተ ጀምሮ የራሱ ስልጣንና ሀላፊነቶች ያለው ተቋም ሲሆን በዚህ ተግባርና ሀላፊነቶች በአስተዳደሩ ላይ ምን እየተሰራ ነው፣ የሚሰሩ የኮንስትራክሽን ስራዎች በኢትዮጲያ ህንጻዎች ቁጥር 624/2001 እንዲሁም በሚኒስተሮች ምክር ቤት መመሪያ ደንብ ቁጥር 293/2003 እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ ቁጥር 5/2009 የመሳሰሉትን በአስተዳደር ደረጃ ማስተግበር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ bበዚህም ለህብረተሰቡ ጤናማ ለከተማው የትራፊክ ንቅስቃሴ ምቹ የሆነና ተወዳዳሪ የሆነች ከተማን ከመፍጠር አንፃር ተቋሙ ከተማው ያቀዳቸውን የአካባቢ ልማትና መዋቅራዊ SP እና LDP ፕላኖችን የማስፈፀም ሀላፊነትና ተግባርና ስልጣን ተሰቶት የተቋቋመ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተዘጋጀው የግንዛቤ መድረክ ላይም የድርጅት አመራሮች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና በየደረጃው እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ አመራሮችን በመጥራት መመሪያና ህገ ደንቦችን በአዎጆች ዙሪያ ባለ ስልጣን መስሪያቤቱ የተቋቋበት አዋጅ ቁጥር 33/2006 በሚገባ አውቆና ተረድቶ ለተቋሙ ራዕይና ስኬት የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አቶ ኤፍሬም አብራርተዋል፡፡
ያለ ግንባታ ፍቃድ የሚገነቡ ግንባታዎችን እስከ ማፍረስና ማስተካከያዎችን እስከ መስጠት በስተት የተገነቡ ግንባታዎችን በነዚህ አዋጆች ተጠቅመን እንዲስተካከሉ አቅጣጫ እስከመስጠት ያለ ስልጣን ስላለ ልንተገብረው ይገባናል ብለዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የህግ አካላት ከተቋሙ ጎን ሆነው ሰላማዊ የሆነና ለህብረተሰቡ ተስማሚ ለአካል ኩዳተኞች ምቹ የሆኑ ህንፃዎች በአስተዳደሩ ላይ ይበልጥ ለመስራት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡ ቅጣትና እርምጃዎችን ከመውሰድ በፊት ህብረተሰቡና አመራሩ ላይ ግንዛቤ መፈጠር አለበት የሚል አቋም ይዘን ነው ዛሬ መድረኮች የዘረጋነው ብለዋል፡፡
በመሬት ወረራና ካርታ ኖሮት ያለ ግንባታ ፍቃድ የሚገነቡ ህንጻዎች ህገ ወጥ ግንባታዎች የሚባሉ እንደሆኑ የገለፁት አቶ ኤፍሬም በምን አይነት ሁኔታ ነው ግንባታውን መጠቀም ያለብኝ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ህብረተሰባችን ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል ብለዋል፡፡
በሚቀጥሉት አስር አመታት አስተዳደራችን ምን መምሰል አለባት የቱ ጋር ነው የመኖሪያ ህንፃዎች መሰራት ያለባቸው የሚለውን በፕላን የተቀመጠ ሲሆን ፕላኑ ወደ መሬት እንዲወርድ ከማድረግ አንፃር ሰፊ ስራ ተቋማችን ይጠበቅበታል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ዛሬ ላይ የተጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ከአመራሩ ጋር ሲሆን በቀጣይ ከአስተዳደሩ ጋር በቅርበት ሆነን እየሰራን በየ ህብረተሰብ ክፍሉ ህገ ወጥ ግንባታዎችን በተቀናጀ መንገድ የማስቀረት ስራ ይሰራል፡፡ ህብረተሰቡ ከተቋማችን ጎን ሆኖ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን የማስገንዘብ ስራ በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኤፍሬም ግርማይ አብራርተዋል፡፡
በከተማ መሰረተ ልማት ፕላን ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ህግ ጉዳይ ባለሞያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ሰይፉ በህንጻ አዋጅ ደንብና መመሪያው ላይ በተለይ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ትኩረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን ሰተዋል፡፡ በመጨረሻም በተሳታፊዎች አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ተጠናቋል።


