የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በተለያዩ መስኮች ተቀራርቦ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በተለይም ካለፋት ሦስት ዓመት ወዲህ በተለይ በአቅም ግንባታ ፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
አሁን ደግሞ ለቀጣይ ሦስት ዓመት የሚቆይና አስተዳደሩን ድህንትና ስራአጥነትን በመቀነስ ልማትና እድገት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚያግዙ ስራዎች በተለያየ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ላይ በጋር መስራት እንዲያስችላቸው የጋራ የመግባቢያ ስምነት ዩኒቨርሲቲውና አስተዳደሩ አድርገዋል፡፡
የጋራ የመግባቢያ ሰነዱን በድሬደዋ አስተዳደር በኩል ምክትል ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሀርቢ ቡህ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል ደግሞ የዩኒቨርሲቲተው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ተፈራርመዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን የጋራ የመግባቢያ ስምነቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት በሁለቱ ወገኖች መካካል በጋራ አቅዶ ለመስራት ስምነት ላይ መድረሱ በተለይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደሩን እስትራቴጂካሊ ለማገዝ ያስችለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሁለቱ ወገኖች ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ግንኙነታቸው እንዲጠናከር ያደርጋል ብለዋል፡፡


