በፌደራልና በክልሎች የሚከናወኑ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራዎች ዕቅድ በተናበበና በተቀናጀ መልኩ እንዲፈፀሙ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ልማት ዳሮክቶሬት እና የፌደራል የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽ ቴክኖሎጂ ዳሮክቶሬት በመቀናጀት በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ የስራ የስምምነት ፊርማ መድረክ ተካሄደ፡፡ የፊርማ ስነስርዓቱ ከዚህ በፊት በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጠሪ እና የክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማት በ2015 በጀት ዓመት በጋራ ሊከናወኑ በለዩት የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራዎች ዕቅድ ትስስር ውይይት መድረክ መሰረት ያደረገ ነው።

    የጋራ እቅዱና የስራ ስምምነት ፊርማ ዋና ዓላማው በሀገር ደረጃ በዘርፉ ያሉ ተቋማቶች ተናበው እንዲሰሩ በማድረግ መሆኑ በስነስረአቱ ላይ ተገልጿል።ግልጽ፤ ወጥ እና ቅንጅታዊ አሰራር እንዲኖር በማድረግ ማህበረሰቡን ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ብሎም ያሉ ውስን ሀብቶች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ ሰላምና ዲሞክራሲያዊ አንድነትን በማጠናክሩ ረገድ ጉልህ ድርሻ ለማስቻልም እንደሆነ ተመላክቷል።

    ይህ ስምምነት በተለይም በዘርፉ በሀገር ደረጃ የተመዘገቡ ውጤቶችን ያጠቃለለ ሀገራዊ ፋይዳዎችን በትክክል ለማሳየት የሚያስችል ሪፖርቶችን ለማዘጋጀት የሚያስችልና መግባባት በተደረሰባቸው ዕቅዶች ላይ ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንዲደረግ የሚያስችል ብሎም በማስፈፀም ሂደት ላይ ለሚከሰቱ ክፍተቶች ተጠያቂነት እንዲኖርና የሚያደርግ ነው ተብሏል።