የድሬዳዋ አስተዳደር ብዙ አገልግሎት የሚሰጠውን የሲቪክ ሴንተር ግንባታን ለማጣነቀቅ ከቻይናው CCECC ጋር ውል ፈፀመ።

    በአስተዳደሩ የተለየ ትኩረት ተሰጥቷቸው በ2015 ዓ.ም እንዲጠናቀቁ ከሚጠበቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው የሲቪክ ሴንተር ግንባታ ነወ፡፡

    ፕሮጀክቱ ለኢንተርናሽናል ተቋራጭ መሰጠቱና ቅድመ ዝግጅቶች በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ያለበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው ተብሏል፡፡

    በተለይ ለስራው እንቅፋት የነበሩት የዲዛይን ችግር መሻሻሎች በተገቢ ትኩረት የተሰሩ ሲሆን የሲሚንቶ እጥረት ችግር እንዳይገጥመው ፕሮጀክቱ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

    ፕሮጀክቱ የተለያዩ የስብሰባ እና የኮንፍረንስ አዳራሾች ያሉት፤ለኪነጥበብ ስራ የሚያገለግሉ ክፍሎች ፤ለቢሮ እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች ፤በቂ የመኪና ማቆሚያና ካፍቴሪያ የያዘ ፕሮጀክት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡