በድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የአስተዳደሩን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሳደግ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት በዛሬው ዕለት ውይይት አካሄደ፡፡ በመድረኩ ላይ ከድሬዳዋና ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲዮች የተወጣጡ ተወካዮች እና በአስተዳደሩ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ተሳትፈዋል ፡፡
ድሬዳዋ በኢንዱስትሪ ልማት ለማሳደግ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ስራዎች መካከል የነጻ ንግድ ቀጠና ይጠቀሳል ፡፡ በአስተዳደሩ የተጀመረው የነጻ ንግድ ቀጠና ከኢትዮጵያ የመጀመሪያው የነጻ የንግድ ሲሆን ይህም ለድሬዳዋ ይዞ የሚመጣው እድል ከፍተኛ በመሆኑ በኢንዱስትሪም ዘርፍም የነጻ የንግድ ቀጠናው የሚያመጠው ትሩፋቶች ግዙፍ ናቸው፡፡
የነጻ የንግድ ቀጠና ከአለም ንግድ ጋር በቀጥታ ያስተሳስረናል፡፡ ስለዚህ ባለን አቅም ያለንን ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ለውድድር ዝግጁ መሆን የህልዉና ጉዳይ ይሆናል፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ፤ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ አብዲ ሙክታር የአስተዳደሩን ኢንዱስትሪ በሚፈለገው ደረጃ ተወዳዳሪና እንዲሆኑ በስራቸው ዉጤታማ እንዲሆን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መታገስ ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ምክትል ቢሮ ኃላፊው ይሄንን ተግባራዊ ለማድረግ በቅርበትና በቅንጅት ለመስራት ያስችለን ዘንድ በአስተዳደሩና በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ከፍተኛ የትምርት ተቋት ጋር የስራ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመን ስራ እንጀምራለን ብለዋል፡፡ በዚህ መሰረት በድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ፤ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ቴክኒክ እና ሙያ እንዲሁም ከድሬዳዋና ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ኮሚቴዎች ተመርጠው ሥራ የሚጀምሩ መሆኑን ተገልጸዋል፡፡


