በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚሰጠው የትምህርት ብርሃን ምዘና ዛሬ ሰኔ 7/ 2014ዓ.ም በይፋ ተጀመረ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ ምዘናው የሚካሄድ ሲሆን በአሰተዳደራችንም በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር በሚገኙት በገጠር ና በከተማ ት/ቤቶች 2453 ተመዛኞች በመመዘኛ ጣቢያቸው በመገኘት የትምህርት ብርሀን ምዘና ፈተና በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ከቢሮዉ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።


