በድሬዳዋ የ3ኛ ዙር የነዋሪዎች የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና በሁሉም የከተማ እና ገጠር ቀበሌዎች እየተሰጠ ይገኛል።
ከሰኔ 4 – 5/ 2014 ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የነዋሪዎች የአቅም ግንባታ “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ- አዲስ አገራዊ እምርታ” በሚል መሪ ቃል የሚሰጠዉ ስልጠና በከተማ ቀበሌና በገጠር ክላስተር መካሄድ ላይ ይገኛል። በሀገር ደረጃ የተዘጋጀው አዲስ ፖለቲካዊ እይታ – አዲስ አገራዊ እምርታ፣ የአስር አመቱ የፓርቲና የመንግስት እቅድ ላይ የአባላት ሚና፣ ለብልጽግና ጉዟችን የኮሚኒኬሽን ክህሎትና የሚዲያ ሚና እና…


