የሃይማኖት አባቶች 3ኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባትን በመከተብና ለምዕመኖቻቸው ስለ ክትባቱ ግንዛቤን በመስጠት ለዘመቻው ስኬታማነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናገሩ፡፡
3ኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በአስተዳደራችን መጀመሩን ተከትሎ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ ሊቀብርሃንናት ቀለመወርቅ ቢምረው ለዓለም ሃገራትም ይሁን ለሀገራችን እንዲሁም ለአስተዳደራችን የጤና እና የህይወት ስጋት የሆነው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ሞትና ህመም ለመከላከል ፈጣሪ በሰጣቸው ጥበብ ተመራማሪዎች ያዘጋጁልንን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትን መከተብ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዋና…


