ለሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ መሳካት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተገለፀ ።

    የኮቪድ-19 ወረርሺኝ በሽታ በሀገራችን ብሎም በድሬዳዋ አስተዳደር ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በሽታውን ከመከካከልና ከመቆጣጣጠር አኳያ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ። በተለይም የኮቪድ-19 ወረርሺኝ በሽታን ለመከላከል እስካሁን በተከናወኑ ሁሉን አቀፍ የመከላከል ተግባራት ባለፍት ሁለት ዙሮች በተሰጠው የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መከላከያ ክትባት አማካኝነት የወረርሺኙ ስርጭት መጠንና በበሽታው ለከፍተኛ ህመምና ሞት የሚዳረጉ ህሙማን ቁጥርን መቀነስ ተችሏል ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር ከመጋቢት 2013 ዓ.ም አንስቶ ብቻ እስካሁን ድረስ በሁለት ዙሮች በተሰጠው የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መከላከያ ክትባት ከ 180 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ክትባቱን የወሰዱ ሲሆን በቀጣይም ከ ሰኔ 2 እስከ ሰኔ 11 2014 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው ሶስተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻም ከ 95 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ለመከተብ እንደታቀደ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ለምለም በዛብህ ተናግረዋል ።
    በመመሪያ ቁጥር 882\2014 ዓ.ም መሰረት ሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞቻቸውን የማስከተብ ሀላፊነት ያለባቸው በመሆኑ በሁሉም የከተማና የገጠር ቀበሌዎች በሚገኙ የጤና ተቋማት ክትባቱ የሚሰጥ በመሆኑ እድሜያቸው ከ 12 አመት በላይ የሆኑ ነዋሪዎች በሙሉ ክትባቱን መውሰድ እንዳለባቸው ወ\ሮ ለምለም በዛብህ ተናግረው ለዚህም ክትባት ዘመቻ መሳካት በአስተዳደሩ የሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም መላው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች የሚጠበቅባቸው ሀላፊነት መወጣት እንዳለባቸውም ተናግረዋል ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ-19 ወረርሺኝ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ አስፈላጊውን ሁሉ የጥንቃቄ ስራዎች ሊተገብሩ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ለምለም በዛብህ በዛሬው እለት ለሚዲያ አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል ።