በመስዋእትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል በሚል መሪ ቃል የፖሊስ የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም የሀገሪቱ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል ።
በዚህ ደማቅ ክብረ በአል ላይ ከፍተኛ ጀብድ የፈፀሙ የፖሊስ አመራር እና አባላት የክብር ሜዳይ ሽልማት የተሸለሙ ሲሆን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምርያ አዘዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የላቀ ስትራተጂ አመራር በመስጠት የክብር ሜዳይ እንዲሁም ም/ኮ ውቢት በፍቃዱ በሰጡት የላቀ አመራር ተሸላሚ ሆነዋል።
ኮሚሽነር አለሙ መግራ የተዘጋጀላቸውን ይህንኑ የሜዳልያ ሽልማትም በክብር ከሀገሪቱ ጠ/ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል::
ድሬ ፖሊስ ሚዲያም ለመላው የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራር እና አባላት ፣ለመላው ማህበረሰባችንናንየድ/ድል አስተዳደር እንዲሁም አጋር የፀጥታ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ ያለን ለማለት ይወዳል::


