የድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡር ያለዉን እምቅ ሀብት በመጠቀም ለከተማዋ ብሎም ለምስራቅ ኢትዮጲያ ኩራት የሆነ ተቋም ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

    በአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የተመራ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ አመራሮች የድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡርን ጎብኝተዋል።በቅርቡ የሚኒስትሮች ም/ቤት መጋቢት 24 ቀን 2014 ባሣለፈዉ ዉሣኔ የድሬደዋ አስተዳደር ከድሬደዋ እስከ ደወሌ ድረስ ያለዉን የምድር ባቡር ንብረት በባለቤትነት እንዲያስተዳድር መወሠኑ የሚታወስ ነዉ።በጉብኝቱ ላይ የአስተዳደሩ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊን ጨምሮ የንብረት ርክክብ ኮሚቴ አባላትና የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል።
    ዘገባው ድሬዳዋ ብዙሀን መገናኛ