የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ለውጥ እያመጣ ነው የድሬዳዋ ነዋሪዎች
የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም በድሬዳዋ የተጀመረው የቅዳሜና የእሁድ ገበያ ሸማቾችና አምራቾችን የሚያገናኝና ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የግብርና ቢሮ በበኩሉ ባለፉት የገበያ ቀናት አበረታች ውጤት በግብርና ምርቶች ላይ እየተገኘ በመሆኑ ገበያው አመቺ በሆኑ በየአካባቢዎች ይስፋፋል ተብሏል፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ቢሮ የህብረት ስራ ማህበራት ግብአትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኑረዲን…


