ለናፍቆት ድሬዳዋ ሳምንት” ለመታደም ወደ ከተማዋ የተለያዩ እንግዶች እየገቡ ነው።

    “ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት”ከሐምሌ 11-15/2014 በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን አስተዳደሩ ለድሬ ተወላጆችና ወዳጆች በአሉን በጋራ እናክብር ጥሪ ተቀብለው እንግዶች ወደ ፍቅር ከተማ ድሬደዋ መግባት ጀምረዋል።
    ቀድሞም የድሬዳዋ እሴት የሆነው በፍቅር አብሮ መኖርና አብሮ መብላት ፍቅራቸውንና ናፍቆታቸውን እየገለፁ የድሬ ወጣቶች ለበአሉ የሚገቡ እንግዶችን በልዩ ናፍቆት አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛሉ።