የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ አስተዳደር ባህል ና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ የባህል እሴት ግንባታ ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
የባህል ና ስፖርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ አስተዳደር ባህል ና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር “የባህል ዕሴቶቻችን ለዜጎች ስብዕና ግንባታ“ በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀት በተለያዩ ባህላዊ ትዕይንቶች ያሸበረቀ ዝግጅት በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ አካሂዷል፡፡
መድረኩን በይፋ የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ክብር ም/ ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ባህል የሀገር ምሶሶ የማንነት መለኪያ መሰሪያ ነው ባህሉን በአግባቡ እና በአወንታዊ ሁኔታ የሚጠቀም ማህበረሰብ ስብዕናውን በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት ይችላል ያሉት ከንቲባው ባህል የማህበረሰብን ማንነት በበጎ መልኩ በመቅረጽ ረገድ ያለው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የባህል እሴቶች የዜጎችን በተለይም የወጣቶችን ስብዕና በጥሩ ሁኔታ በመገንባት ፣በስነ ምግባር የታነጹና ለሀገራቻው ጠቃሚና ትውልድ ተሻጋሪ ስራ እንዲሰሩ ከማድረግ አንጻር ሚናቸው የጎላ ነውም ብለዋል፡፡
ከአወንታዊ ባህል ባፈነገጠ መልኩ በአሁን ወቅት ከማህበረሰቡ ባህል ና አስተሳሰብ ጋር አብረው የማይዛመድ መጤ ባህሎች እየተስፋፉ የትውልዱን አወንታዊ አንድነት የሚገቱ ባህሎች እና ድርጊቶችን ለማስቀረት ሰፊ መሰል የግንዛቤ ማሰጨበጥ ስራዎች መስራት እንደሚገባም ጭምር ክብር ከንቲባው ጠቁመዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ባህል ና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ በበኩላቸው ድሬዳዋ የበርካታ የተለያዩ ባህል እሴት ትውፊት ና ወግ ያላቸው ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩባት ልዮነቶቻቸውን ውበቶቻቸው ና የአንድነታቸው ምሶሶ የሆነላቸው ህዝቦች ማሳያ ከተማ መሆኗዋን ገልጸው እነዚህን ውብ ባህሎቿዋን ጠብቆ በማቆየት እና የባህል እሴቶች እንዲጎለብቱ ለማድረግ በርካታ የግንዛቤ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዉ በዛሬዉ ቀን በድሬዳዋ አሰተናጋጅነት ሀገር አቀፍ የባህል እሴት ግንባታ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ የቱሪዝሙ ዘርፍ እንዲነቃቃ ከማስቻሉም በላይ በዘርፉ የሚገኝው ገቢ ለከተማው ኢኮኖሚያዊ እድገት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ ሀገራችን ካላት እምቅ የባህል እሴቶቻችን መካከል በዋናነት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንባታ መሰረት የሆኑት የስራና የቁጠባ ባህላችን እድር፤እቁብ ደቦ እነዚህን በማጎልበት ወጣቱ እንዲጠቀምባቸውና የስራና የቁጠባ ልምዶቻችን በማጠናከር ሁሉን አቀፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በትጋት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በምክክር መድረኩም ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን በረዳት ፕሮፌሰር ዝናቤ ስዩም የባህል ዕሴቶቻችን ለወጣቶች ስብዕና ግንባታ ያላቸው ሚና ፣ በእጩ ዶክተር ሀይለሚካኤል ደረሰ የስራ ና የቁጠባ ባህላችን ለማጠናከር የዜጎች ሚና እንዲሁም በረዳት ፕሮፌሰር ጃራ ሰማ አሉታዊና መጤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የህብረተሰቡ ድርሻ በሚል ርዕስ ና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎች በምሁራኑ ቀርበውው ከመድረኩ ተሳታፊዎች ጋር በጥልቀት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመድረኩም በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በየደረጃው የሚገኙ የፌደራል ና የሚንስተር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሴት ፌድሬሽን አመራሮች ፣ወጣቶች፣ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


