የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚነት ምዝገባ
በሂደት ላይ የሚገኘውን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በቴክኖሎጂ በማገዝ ተግባራዊ ለማድረግ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሠራን እንገኛለን።
በዚህም መሠረት በድጎማው ተጠቃሚ እንድትሆኑ የተለያችሁ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አገልግሎቱ የሚሰጠው በቴሌብር አማካኝነት ስለሆነ በኢትዮ ቴሌኮም የሸያጭ ማዕከላት ዋና ወይም ቅጂ ሊብሬ እንዲሁም የታደሰ መታወቂያ በመያዝ የተሸከርካሪውን ባለቤት የስልክ ቁጥር በማሳወቅ የቴሌብር አገልግሎት ምዝገባ ከወዲሁ እንድታከናውኑ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን እንድታሟሉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ


