በአስተዳደሩ 9ኙ ከተማ ቀበሌዎች እና በ4ቱ ገጠር ክላስተሮች የታቀፉ 38 ገጠር ቀበሌዎች ትላንት መካሄድ የጀመረው የ3ኛ ዙር የነዋሪዎች የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።
ከሰኔ 4 – 5/ 2014 ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የነዋሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው አዲስ ፖለቲካዊ እይታ – አዲስ አገራዊ እምርታ፣ የአስር አመቱ የፓርቲና የመንግስት እቅድ ላይ የአባላት ሚና፣ ለብልጽግና ጉዟችን የኮሚኒኬሽን ክህሎትና የሚዲያ ሚና እና የፓርቲ ተቋማዊ ግንባታ ዙሪያ በተዘጋጀውን ሰነድ ግንዛቤ ከማሳደግ በተጨማሪም ሰነዱን አውቆ ከመተግበር አንጻር የአባሉ ሚና ምን መሆን እንዳለበት መግባባት የተደረሰበት ስልጠና እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።
ከስልጠናው ጎንለጎን ሰኔ 2 – 11/2014 መሰጠት የተጀመረው 3ኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ሰልጣኞችም ተሳታፊ ሆነዋል ሲል


