ከሰኔ 4 – 5/ 2014 ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የነዋሪዎች የአቅም ግንባታ “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ- አዲስ አገራዊ እምርታ” በሚል መሪ ቃል የሚሰጠዉ ስልጠና በከተማ ቀበሌና በገጠር ክላስተር መካሄድ ላይ ይገኛል።
በሀገር ደረጃ የተዘጋጀው አዲስ ፖለቲካዊ እይታ – አዲስ አገራዊ እምርታ፣ የአስር አመቱ የፓርቲና የመንግስት እቅድ ላይ የአባላት ሚና፣ ለብልጽግና ጉዟችን የኮሚኒኬሽን ክህሎትና የሚዲያ ሚና እና የፓርቲ ተቋማዊ ግንባታ ዙሪያ የተጨመቀ አራት ሰነዶች ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።
በቀረቡ ሰነዶች በአስተዳዳራችን የሚገኙ ሁሉም የፓርቲያችን አባላት ስልጠናውን በመውሰድ የጋራ ግንዛቤ እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል፡፡


