ለቀጣይ ስድስት ወራት የኤች አይ ቪ ተጋላጭ ማህበረሰብ የምርመራ ዘመቻ ለማድረግ የንቅናቄ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

    እንደ ሀገር የተጀመረውን የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭ ማህበረሰቦችን ምርመራ እና መፍትሄ ማመቻቸትና የንቅናቄ አቅጣጫ መርሀ ግብር በዛሬው እለት በድሬደዋ አስተዳደር ከባለድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
    በመረሀ ግብሩ ላይ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰይድ እንደተናገሩት
    የኤች አይ ቪ ኤድስ ታማሚዎች እንደ ሀገር ቁጥራቸው አየጨመረ በመምጣቱ ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመለየት ከፌደራል የሚላኩትን መመርመሪያዎች በአግባቡ ለመጠቀም የቅድመ ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል ፡፡
    ምክትል ሀላፊው ከዚህም ጋር በማያያዝ ቀደም ባሉት ጊዜያት ታማሚዎችን ወደ ህክምና በማምጣት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግ ክፈተት አለብን በማለት በዚህ የዘመቻ ስራ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የተለዩ ማህበረሰቦችን በመመርመር በሽታው በውስጣቸው የተገኘባቸውን ታማሚዎች አገልግሎቱን በአግባቡ እንዲያገኙ ከባለብርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡
    ከዚህም በተጨማሪ የዘመቻውን ስራ በየሳምንቱ በመፈተሽ ውጤታማና የታቀደውን እቅድ ለማሳካት እንደሚሰሩም ነው የገለፁት፡፡
    በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር የኤች አይ ቪ ኤድስ አስተባባሪ ሲ/ር ዮዲት ተገኝ በበኩላቸው እንደተናገሩት ኤች አይ ቪ ኤድስ በሚቀጥሉት ጊዚያት በማህበረሰቡ ውስጥ በሽታ ሆኖ እንዳይቀጥል በጤናው ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች ሁሉም ያለሰለሰ ጥረት በማድረግ በዘመቻው የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡ማህበረሰቡ በመመርመር እራሳቸውን ማወቅ አለባቸውም ብለዋል፡፡
    የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት በጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስና የአባላዘር በሽታ ፈፃሚ ባለሙያ አቶ ታሪኩ አበበ በድሬደዋ አሁን ያለው የቨይረሱ ስርጭት ከአዲስ አበባና ከጋንቤላ ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ በመገኘቷ የዘመቻው ስራ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ቀደም ባሉት አመታት የነበረውን የተለዩ ማህበረሰብ ክፍሎችን ለይቶ የመመርመርና የኤች አይ ቨ ኤድስ የምክር አገልግሎት መጓደል ክፍተቶችን አጠናክሮ በመስራት እቅዱ በተሳካ ሁኑታ እንዲሰራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በመድረኩ መሳተፋቸውን ገልፀዋል፡፡