ቢሮው ከዚም በፊት ለበርካታ ዓመታት እድሳትና ሌሎች አስፈላጊ የካይዘን ለውጦች በተሟላ ሁኔታ አልተደረጉለትም ነበር። ይህንን ሁኔታ ከግምት በማስገባት የቢሮው ማኔጅመንት ተወያይቶ በግላቸው የቻሉትን ያህል በማዋጣትና ቀሪውን አንዳንድ ባለሃብቶችን ድጋፍ በመጠየቅ ቀድም ሲል የነበረውን ሁኔታ መቀየር ያስቻለ ስራ አከናውኗል፡፡
እያንዳንዱ ግብአትና አብዛኛው ድጋፍ የተገኘው ከጥቂት ባለሃብቶች ሲሆን ከመንግስት ካዝና ምንም አይነት ወጪ አልተደረገም፡፡ በዚህ መሰረት 90ሺህ ብር ከባለሃብት የተገኘ ከፍተኛ ድጋፍ ሲሆን ዝቅተኛው 3ሺህ ብር ነው፡፡ ከማኔጅመት አባላት ደግሞ እስከ 7ሺህ ብር የሚሆን ድጋፍ ተሰብስቧል።
በባለሀብቶች የተደረጉት ድጋፎች ፡-
* የመሬት ምንጣፍ
* ቀለም
* አበባ
* 54 ኢንች ቴሌቩዥን
* ፎቶ ፍሬም
* ቢልቦርድ እና ሌሎች ድጋፎችን ያካተተ ነው።
አጠቃላይ የተደረገ ድጋፍ 205,000 ብር የሚጠጋ ነው።በአጠቃላይ ቢሮው እያደረገ ላለው ለውጥ ድጋፍ ላደረጋቹ ባለሐብቶች ከወዲሁ በቢሮና በሰራተኞች ስም እጅግ እናመሰግናለን።
የድሬደዋ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ


