ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የጤና ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህና የት/ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሃመድ ሲሆኑ ተማሪዎች ኮሮናን ለመከላከል የሚደረጉ የጥንቃቃቄ ተግባራትን በሚገባ እንዲተገብሩና የገፅ ለገፅ ትምህርት በበሽታው ስርጭት መስፋፋት ዳግም እንዳይቁዋረጥ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል::
ተማሪዎች በት/ቤትና ከቤት ውጭ ባላቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ማስክ በመልበስ፣ የእጃቸውን ንፅህና በመጠበቅና አካላዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ ራሳቸውንና ሌሎችን ከበሽታው እንዲታደጉም ሀላፊዎቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::
ከፕሮግራሙ በይፋ መጀመር በኃላም ተማሪዎችና የት/ቤቱ ማህበረሰብ በት/ቤቱ ዙሪያ ባሉ ቦታዎች በመዘዋወር ለማህበረሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን የማስተላለፍ ስራ ሰርተዋል::
የንቅናቄ ፕሮግራሙ በቀጣይ በሁሉም ት/ቤቶች የሚካሄድ ይሆናል::
ምንጭ : ድሬዳዋ ጤና ቢሮ


