ከንቲባው ድምፃቸውን የሰጡት በአስተዳደሩ ወረዳ 04 በሚገኘው ምርጫ ጣቢያ አንድ ነው።
ከንቲባ ከድር ጁሃር ድምፅ በሰጡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዜጎች በሕገ-መንግስቱ የተሰጣቸውን የመምረጥ መብት በአግባቡና በሃላፊነት ስሜት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በአገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን የገለጹት ከንቲባው፤ መላው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥና የአገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ መራጭነት ካርድ የወሰዱ ዜጎች ሁሉ በሂደቱ ላይ በነቂስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በምርጫ ጣቢያው የነበረውን ድባብ በተመለከተም፤ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አዛውንቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለዳውን ጀምሮ በሰላማዊ ሁኔታ ሰልፍ በመያዝ ድምፅ በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።


