በድሬዳዋ አስተዳደር ከመሬት ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም ይነሱ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፈታት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

    የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከዚህ ቀደም በነዋሪው ህብረተሰብ ይነሱ የነበሩ የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አኳያ በተለይም ከመሬት ይዞታ፣ ከመሬት ዝግጅት እንዲሁም ለልማት ተብለው ተወስደው ነገር ግን ረጅም አመት ታጥረው የነበሩ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ ከማስገባት አኳያ የተለያዩ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
    ከመሬት ዝግጅት ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም በርካታ ስራዎች ቢሰሩም ነገር ግን የተለያዩ ቅሬታዎች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመኖራቸው ምክንያት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት አሁን ላይ የሚዘጋጁ መሬቶችን ቅሬታዎችን ለመፍታት ከማድረግ በዘለለ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠትና አስፈላጊውን በጀት እንዲመደብ በማድረግ የመሬት ዝግጅቱን የማዘጋጀትና መሬቱን የማስተላለፍ ስራ በሰፊው እንደሚሰራም የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡
    በድሬዳዋ አስተዳደር ለልማት ተብለው የተወሰዱ ነገር ግን ለረጅም አመት ታጥረው የቆዩ 135 ሄክታር መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ በማድረግ ለአልሚዎች መተላለፍ መቻሉን አቶ ገበየሁ ጥላሁን ተናግረው ባለሀብቶች መሬት ወስደው አልምተው ለዜጎች ሰፊ የስራ እድልን ሊፈጥሩ የሚችሉበትን አጋጣሚዎች ነገር ግን መሬቶችን አጥረው ማስቀመጥን ለማስቀረት በመሰራት ላይ እንደሚገኝም ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
    አቶ ገበየው አክለውም ከዚህ ቀደም 135 ሄክታር መሬት መክኖ ወደ ሌሎች አልሚዎች የተላለፈ ሲሆን ከዚህ ውስጥም ቅሬታ የነበረባቸውና አላግባብ ለመከነባቸው 9 አልሚዎች ለካቢኔ ቀርቦ እንዲመለስላቸው የተደረገ ሲሆን በዚህም በአሊሚዎች የነበሩ ቅሬታዎች ለመፍታት መቻሉን ተናግረዋል ። ከዚህ በተጨማሪም 46 ሄክታር መሬት በተለያዩ ምክንያት በእጃቸው ይዘው የማልማት ጥያቄ ላቀረቡና ከዚህ ቀደም ከተዘጋጀ መሬት ላይ ለማኑፋክቸሪንግና ለማህበራዊ ዘርፍ ይሆን ዘንድ ለካቢኔ በማቅረብ ማሶሰናቸውን አቶ ገበየው ገልፀው በተለያዩ የአለማችን ሀገራት የሚገኙ የከተማዋ ተወላጆችም በከተማ አስተዳደሩ ላይ እንዲያለሙ የመሬት ዝግጅት ከማድረግ አንስቶ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚደረጉ ተናግረው አልሚዎችም ወደ ስራ በመግባት ከዚህ ቀደም ከውጪ ሀገራት የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረትና በጋራ በመስራ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻልም የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡