“ማህበራዊ እሴቶቻችንን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ25ኛ ጊዜ በአገራችን ለ11ኛ ጊዜ የሚከበረው የአብሮነት ቀን በዛሬው እለት በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረገው የአስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙራድ በደዊ የአብሮነት ቀን ዋነኛ ዓላማ የድሬዳዋ ማህበረሰብ ያፈራውና የገነባውን ጠቃሚ ማህበራዊ ዕሴቶችን መልሶ መገንባት የሚያስችል ተግባራት የሚከናወንበት ይሆናሉ ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ የድሬዳዋ ነባር ባህል እንኳን እየኖሩበት ይቅርና ሳይኖሩበት ተወርቶ የማያልቅ ነው ብለዋል፡፡ የድሬዳዋ ማህበረሰብ የነበራቸው የአብሮነት ተመሳሌት ከምን ጊዜም በላይ በነዋሪዎቿ አንደበት ተነገሮ የማያልቁ ናቸው ብለዋል፡፡
የአብሮነት ቀንን በማስመልከት የድሬዳዋ ማህበረሰብ ያፈራውና የገነባውን ጠቃሚ ማህበራዊ ዕሴቶችን መልሶ ለመገንባት በሚያስችል መልኩ በባለሙያዎች የተዘጋጁ ጥናታዊ ፅሁፎች እና የድሬዳዋ ቀደምት ነዋሪዎች እሴቶቻቸውንና ልምዶቻቸውን በፕሮግራሙ ላይ ለተገኙ ተጋባዥ እንግዶች ቀርቧል፡፡
በፕሮግራሙ ላይም የአስተዳደሩ ከንቲባና የአስተዳደሩ አፈጉባኤ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ ወጣቶችና የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ፕሮግራም በተለያዩ መርሃ ግብር ተከብሮ ውሏል።


