December 4, 2021
16ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ምክኒያት በማድረግ ሚዲያ ጉብኝት ተደረገ፣
16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በድሬዳዋ አስተዳደር አስተናጋጅነት “ወንድማማችነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ነው ። የበዓሉ አንዱ አካል የሆነው የአስተናጋጇ የድሬዳዋ አስተዳደር ታሪካዊ ስፈራና የልማታዊ እንቅስቃሴዎች በሚዲያ ባለሙያዎች ጉብኝት ተደረጓል። በጉብኝቱም መርሃግብር በፋሽስቱ ጣልያን ወረራ ጌዜ ከአርበኞች ጋር በመሰለፍ የተሰውትን የአፍሪካዊያን ወንድሞቻችን መካነ መቃብር ጉብኝተዋል። ዓላማውም አፍሪካውያን…
በድሬዳዋ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መግለጫ አውጥቷል ።
በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሀገራችን ኢትዮጲያ አሁን ላይ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ውይይት በማካሄድ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል ። በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሀገርና ከህዝብ በላይ የሚያስቀድመው አጀንዳ ሊኖር ስለማይችል አሸባሪው የወያኔ ቡድንና ተላላኪዎች እየፈፀሙ ያለውን እኩይ ድርጊት አውግዘው ከህዝባቸውና ከመሪያቸው ጎን እንደሚቆሙም ገልፀዋል ። ውድ ህይወቱን ሳይሰስት በግንባር ለሚፋለመው የመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ…
16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ዋዜማን ታሳቢ በማድረግ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።
በድሬዳዋ የሚካሄደው 16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ዋዜማን ታሳቢ በማድረግ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ የአስተዳደሩ ለፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በልዩ ሁኔታ ተካሂዷል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የእንኳን አደረሳቹ መልእክት አስተላለፉ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ለ16ኛ ጊዜ #ወንድማማችነት ለህብረብሄራዊ አንድነት$ በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተናጋጅነት ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ክብርት አፈ-ጉባኤዋ በመልእክታቸውም ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ በውቢቷና የኢትዮጵ ብሄር ብሄረሰቦች በወንድማማችነትና በፍቅር በሚኖሩባት ትንሿ ኢትዮጵያ ድሬዳዋ መከበሩ ልዩ የሚደርገው ለዘመናት የኢትጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ሲጠይቁ…


